አዳም ረታ

  1. home
  2. Author
  3. አዳም ረታ
አዳም ረታ

13 Published Booksአዳም ረታ

አዳም ረታ በ1950 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። በትምህርት አለም - በጂኦግራፊ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ሁለተኛ (የማስተርስ) ዲግሪውን ደግሞ በውጭ ሀገር አግኝቷል። የሚፅፈው በአብዛኛው አጫጭር ልቦለዶችን ቢሆንም ግጥሞችንም ይፅፋል። በተለያዩ ጊዜያት ግጥሞቹ በተለያዩ መፅሔቶች ላይ ታትመዋል። ያልታተሙ ግጥሞችም አሉት።

‹ማሕሌት›፣ ‹አለንጋና ምስር›፣ ‹እቴሜቴ ሎሚ ሽታ›፣ ‹ከሰማይ የወረደ ፍርፍር›፣ ‹ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ›፣ ‹ሕማማትና በገና› የተሰኙ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ መጽሀፍትን በግሉ አሳትሟል፡፡

የአዳም የረዥም ልብወለድ ሥራ የሆኑት ‹ግራጫ ቃጭሎች› እና ‹መረቅ›ም በብዙ አንባቢዎች ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፡፡

አዳም ረታ በአጻጻፍ ስልቱ ልዩ፣ በቋንቋ አጠቃቀሙ ማራኪ እና በሚያነሳቸው ሀሳቦች ምጡቅ ደራሲ እንደሆነ የስነ-ጽሑፍ ባለሙያዎችና የሥራዎቹ አንባቢዎች ይመሰክራሉ፡